የራያ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ፕሮገራም ዳይሬክቶሬት እና የትምህርት ጥራት ማሻሻያ ዳይሬክቶሬት ያዘጋጁት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የትምህርት ጥራትና አግባብነት፣ የእውቅና አሰጣጥ፣ እድሳት፣ ክትትልና ቁጥጥር ስርዓት እና የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ትምህርት እና ስልጠና ባለ ስልጣን ዝርዝር ተግባራት ለዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ካውንስል አባላት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ታህሳስ 08/ 2017 ዓ/ም በዩኒቨርሲቲው አዳራሽ ተሰጥቷል፡፡
የዩኒቨርሲቲው አካ/ምር/ቴክ/ሽግ/ማህ/አገልግሎት ምክ/ፕረዚደንት ነጋ ዓፈራ (ዶ/ር) በግንዛቤ ማስጨበጫ መርሃ ግብሩ እንደተናገሩት የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ትምህርት እና ስልጠና ባለ ስልጣን የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ እና ተማሪዎች በእውቀት፣ ክህሎት እና ስነ ምግባር ብቁ እንዲሆኑ በርካታ የአሰራር ማሻሻያ እርምጃዎችን እየወሰደ መሆኑን ገልጸው ዩኒቨርሲቲያችን መሰረት ያደረገ የባለ ስልጣኑ መመሪያ በአግባቡ መገንዘብ ይኖርብናል ብለዋል።
የዩኒቨርሲቲው የትምህርት ጥራት ማሻሻያ ዳይሬክተር መምህር ብርሃነ ፀጋይ (ረዳት ፕሮፌሰር) ባቀረቡት ፅሁፍ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የትምህርት ብቃት እና አፈፃፀማቸውን ለማሻሻል እና የትምህርት ጥራት ለማረጋገጥ ውጤት ተኮር የትምህርት መርሃ ግብር በመተግበር ለመማር ማስተማር ምቹ የሆነ ተቋም መፍጠር ይጠበቅብናል በማለት በትምህርት ጥራት ዙርያ የተቋም፣ መምህራን እና ተማሪዎች ሚና እንዲሁም በቀጣይ ምን መደረግ እንዳለበት ዝርዝር ማብራሪያ ሰጥተዋል።
የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ፕሮግራም ዳይሬክተር ቀሲስ ንጉስ መሰለ (ዶ/ር) በበኩላቸው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፍቃድ አሰጣጥ፣ መስፈርት እና ዳግም ምዝገባ፣ ክትትልና ቁጥጥር መመሪያ ፣ ተቋማዊ እና የመርሃ ግብር እውቅና ለማግኘት የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎች፣ የመመሪያው አስፈላጊነት እና ተቋማዊ ግምገማ፣ መዋቅር፣ ሂደት፣ ውጤት እና የምስክር ወረቀት አሰጣጥ ጉዳዮች ዝርዝር ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ከግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናው ተሳታፊዎች የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የትምህርት ጥራትና አግባብነት፣ የእውቅና አሰጣጥ፣ እድሳት፣ ክትትልና ቁጥጥር ስርዓት ዙርያ ለተነሱ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች በሚመለከታቸው የስራ ሃላፊዎች ምላሽ እና ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡
በግንዛቤ ማስጨበጫ መርሀ ግብሩ የመዝጊያ ንግግር ያደረጉት ዶ/ር ነጋ ዓፈራ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የትምህርትና ስልጠና ባለ ሥልጣን በአዋጅ የተሰጠውን የትምህርትና ስልጠና ጥራትን የማረጋገጥ ተልዕኮ ለማሳካት በርካታ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን ጠቅሰው ዩኒቨርሲቲያችን ብቁ መምህራን፣ ቤተ ሙከራ እና የመማሪያ ቁሳቁስ በማሟላት በትምህርት ጥራት በትኩረት እንደሚሰራ ገለጸዋል፡፡
ራያ ዩኒቨርሲቲ ፤ ታህሳስ 09/ 2017 ዓ.ም
ዕውቀት ለማኅበረሰባዊ ለውጥ!
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈፃሚ
**************************************