አስደሳች ዜና ለድህረ ምረቃ መርሐ ግብር የመግቢያ ፈተና (NGAT) ተፈታኞች በሙሉ!

የትምህርት ሚኒስቴር የድህረ ምረቃ ፕሮግራም የመግቢያ ፈተና (NGAT) የምዝገባ ጊዜ ሠሌዳ ባሳወቀው መሰረት በ2017 የትምህርት ዘመን የድህረ ምረቃ መርሐ ግብር ለመማር ፍላጎት ያላችሁ አመልካቾች በራያ ዩኒቨርሲቲ የሚሰጠውን የድህረ ምረቃ መርሐ ግብር የመግቢያ ፈተና (NGAT) ከጥር 7-9/2017 ዓ.ም ስለሚሰጥ በ https://NGAT.ethernet.edu.et ትስስር ገፅ በኩል የፈተና ቦታ “ራያ ዩኒቨርሲቲብር 750 በቴሌ ብር በመክፈል መመዝገብ ትችላላችሁ።
#ተፈታኞች ከምዝገባው በኃላ ለፈተናው አጋዥ ትምህር (Tutorial) እና መጻሕፍት በዩኒቨርሲቲው ይሰጣሉ።

ራያ ዩኒቨርሲቲ ፤ ታህሳስ 15 /2017 ዓ.ም
ዕውቀት ለማኅበረሰባዊ ለውጥ!
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈፃሚ
************************************