የጥምቀት በዓል ምክንያት በማድረግ በራያ ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት በራያ፣ አክሱም፣ ዓዲ ግራት እና መቐለ ዩኒቨርሲቲዎች መካከል ከጥር 07-10/ 2017 ዓ.ም እየተካሄደ የነበረው የማስ ስፖርት ውድድር በስኬት ተጠናቀቀ።
በውድድሩ ንግግር ያደረጉት የየራያ ዩኒቨርሲቲ ፕረዚደንት ታደሰ ደጀኔ (ፕሮፌሰር)፤ ማስ ስፖርት ለሰላም፣ለ አንድነት፣ ለጤንነትና ለስራ ውጤታማነት ትልቅ አስተዋጽኦ አለው ብለዋል።
የውድድሩ ዓላማ በዩኒቨርሲቲዎቹ መካከል ያለውን ወዳጅነት ለመፍጠር እና ቀጣይነት ባለው መልኩ ለማጠናከር ነው።
በውድድሩ መቐለ ዩኒቨርሲቲ የመረብ ኳስ እና እግር ኳስ ዋንጫ አሸናፊ ሆኗል።