በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት እየተካሄደ የሚገኘው የ2017 ዓ.ም የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የተማሪዎች ስፖርት ፌስቲቫል እየተሳፈ የሚገኘው የራያ ዩኒቨርሲቲ እግር ኳስ ክለብ የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ እግር ኳስ ክለብ አቻውን 3 ለ 2 በማሸነፍ ሙሉ 3 ነጥብ በማሳካት ምድብ 12ን መምራት ጀምሯል።
የራያ ዩኒቨርሲቲ እግር ኳስ ክለብ አሠልጣኝ መምህር ሃፍተማርያም ከበደ ለዩኒቨርሲቲው ህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አሥፈጻሚ ጽ/ቤት በሰጡት አስተያየት ዛሬ ጥር 18/ 2017 ዓ.ም ከ8: 00 ጀምሮ በአዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የተካሄደ የሁለቱም ክለቦች ጨዋታ ማራኪ እና አዝናኝ እንዲሁም ተመጣጣኝ ፉክክር የታየበት ጨዋታ የነበረ ቢሆንም ከጨዋታው 3 ነጥብ መውሰዳችን ደስተኞች ነን ብለዋል።
የሁለቱም ክለቦች ጨዋታ የራያ ዩኒቨርሲቲ ፕረዚደንት ፕሮፌሰር በቦታው ተገኝተው የተመለከቱት ሲሆን የራያ ዩኒቨርሲቲ ጎሎችን ያስቆጠሩ ተጨዋቾች አሚር፣ መርኢድ እና ደቦል አስቆጥረዋል።
የስፖርት ፌስቲቫሉ እስከ ጥር 27/ 2017 ዓ.ም የሚቀጥል ሲሆን የራያ ዩኒቨርሲቲ እግር ኳስ ክለብ ነገ ጥር 19/ 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8: 00 ሁለተኛ የምድብ ጨዋታውን ከአምቦ ዩኒቨርሲቲ እግር ኳስ ክለብ ጋር የሚያደርግ ይሆናል።