በራያ ዩኒቨርሲቲ ሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ከተፈተኑት 96.25% ፈተናውን አልፈዋል።

በሃገር አቀፍ ደረጃ ከጥር 26 – 30/ 2017 ዓ.ም በተሰጠው የ2017 ዓ.ም አጋማሽ የቅድመ ምረቃ የተማሪዎች የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ራያ ዩኒቨርሲቲ ካስፈተናቸው ተፈታኞች 96.25% አሳልፏል።
ይህ ትልቅ ውጤት እንዲመዘገብ የላቀ አሥተዋጽኦ ላበረከቱት አካላት ዩኒቨርሲቲው ምሥጋናውን ያቀርባል።

እንኳን ደስ አላችሁ ደስ አለን!


ራያ ዩኒቨርሲቲ ፤ የካቲት 07/ 2017 ዓ.ም
ዕውቀት ለማኅበረሰባዊ ለውጥ!
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈፃሚ
********************