ይህ የተገጸው በራያ ዩኒቨርሲቲ የራያ ባህል እና ምርምር ማዕከል በትግራይ ደቡባዊ ዞን ከሚጉኙ የባህል እና ቱሪዝም ቢሮ ሠራተኞች እና ባለሙያዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የኪነ ጥበብ፣ የማህበረሰብ፣ የሀይማኖት ተወካዮች እንዲሁም ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ዛሬ የካቲት 23/ 2017 ዓ/ም በመኾኒ ከተማ ባካሄደው የምክክር መድረክ ነው።
የምክክር መድረኩ ቁልፍ ዓላማ የሚዳሰሱ እና የማይዳሰሱ የራያ ቅርሶች፣ ባህል እና ትውፊት፣ ስነ-ጥበብ፣ ቋንቋ፣ ስነ-ጽሑፍ ታሪክ፣ ሀገር በቀል ዕውቀቶች፣ ኪነ ጥበብ፣ አኗኗር ዘይቤ፣ ታሪካዊ እና ተፈጥሮአዊ የቱሪዝም መስሕቦች መሰረት ያደረገ ጥናትና ምርምር በማካሄድ መሰነድ እና ለማሳደግ ነው።
የራያ ባህል እና ምርምር ማዕከል አስተባባሪ መምህር ካሕሳይ ቸኮለ (ረዳት ፕሮፌሰር)፤ የማዕከሉ ተልዕኮ፣ ዓላማ፣ ራዕይ፣ የባለድርሻ አካለት ሚና፣ በማዕከሉ የሚሰጡ አገልግሎቶች እና ማዕከሉ እያከናወናቸው ያሉ ቁልፍ ተግባራት ገለጻ አድርገዋል።
ማዕከሉ በዋናነት የራያ ባህል፣ ቋንቋ፣ ስነ ጽሑፍ፣ ኪነ ህንጻ፣ ሙዚቃ፣ ስነ ጥበብ፣ ፍልስፍና፣ ስነ-ጽሑፍ፣ ታሪክ፣ ቅርስ ሀገር በቀል ዕውቀቶች ለማሳደግ የተለያዩ የምርምር እና ስነዳ ስራዎች እየሰራ እንደሚገኝ መምህር ካሕሳይ አክለው ገልጸዋል።
በመጨረሻም ከተሳታፊዎች በተደረገ ውይይት፤ ድንቅ መገለጫዎች ያሉት የራያ ባህል ለትውልድ ለማስተላለፍ እና የማህበረሰቡን ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ፣ ምጣኔ ሃብታዊ እና ስነ ልቦናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በዘርፉ የሚታዩ የአስተሳሰብ ክፍተቶች፣ የሠው ኃይል እጥረት እና የበጀት ችግር ውጤት ተኮር የግንዛቤ ማስጨበጫ መርኃ ግብሮች በማዘጋጀት በቅንጅት መስራት እንደሚያስፈልግ ተገልጿል።




********//********************************
ራያ ዩኒቨርሲቲ ፤ የካቲት 23/ 2017 ዓ.ም
ዕውቀት ለማኅበረሠባዊ ለውጥ!
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አሥፈጻሚ
*******//*********************************