ዩኒቨርሲቲው በ2017 ዓ.ም ሁለተኛ ሩብ ዓመት በመማር ማስተማር፣ ምርምር፣ ቴክኖሎጂ ሽግግር እና ማህበረሰብ ጉድኝት ዘርፍ የቁልፍ ተግባራት አፈጻጸም አመላካቾች (KPI) መሰረት በማድረግ የሰራቸው ስራዎች እና እያከናወናቸው ያሉ ቁልፍ እና ዓበይት ተግባራት ከመምህራን ጋር ዛሬ የካቲት 25/ 2017 ዓ.ም ውይይት አካሄደ።
በውይይቱ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የዩኒቨርሲቲው ፕረዚደንት ፕሮፌሰር ታደሰ ደጀኔ የዩኒቨርሲቲያችን ስራዎቹን የቁልፍ ተግባራት የአፈጻጸም አመላካቾች (KPI) መሰረት በማድረግ እየሰራ መምጣቱን የሚታወቅ ሲሆን በቀጣይም ሁሉም ስራዎቻችን በመደራጀት እና በመቀናጀት በዕቅድ ተመስርተን በየጊዜው እየፈተሽን ከተቋሙ ዕቅድና የትኩረት መስኮች ጋር አቀናጅተን ስኬታማ ስራ መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል።
የራያ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ መርኃ ግብር ዳይረክተር (APD) ዶ/ር ንጉስ መሰለ የቁልፍ ተግባራት አፈጻጸም አመላካቾች (KPI) መሰረት በማድረግ ራያ ዩኒቨርሲቲ በ2017 ዓ/ም ሁለተኛ ሩብ ዓመት በመማር ማስተማር ያከናወናቸው ቁልፍ እና ዓበይት ተግባራት፣ የነበሩ ጠንካራ ጎኖች፣ ያጋጠሙ ችግሮች የተወሰዱ መፍትሄዎች እንዲሁም በቀጣይ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮችዝርዝር ገለጻ አድርገዋል።
የራያ ዩኒቨርሲቲ ምርምር፣ ሕትመት፣ ሥነ ምግባር እና ሥርጸት ዳይሬክተር መምህር ተመስገን ተስፋይ (ረዳት ፕሮፌሰር) በበኩላቸው ዳይሬክቶሬቱ የቁልፍ ተግባራት አፈጻጸም አመላካቾች (KPI) መሰረት በማድረግ ዳይሬክቶሬቱ በምርምር አጀንዳ፣ በጀት፣ ውጤት፣ ህትመት፣ የሴት መምህራን ተሳትፎ፣ እየተሰሩ ያሉ ፕሮጀክቶች፣ እያጋጠሙ ያሉ ችግሮች፣ ለቀጣይ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች እና የተሰጡ የዓቅም ግንባታ ስራዎች ገለፃ አድርገዋል፡፡
የራያ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ ጉድኝት ዳይሬክተር መምህር ደባሲ ግደይ፤ የቁልፍ ተግባራት አፈጻጸም አመላካቾች (KPI) መሰረት በማድረግ ዳይሬክቶሬቱ በ2017 ዓ/ም ሁለተኛ ሩብ ዓመት በትምህርት ቤቶች ድጋፍ፣ መንገድ እና ትራፊክ ደህንነት፣ አዕምሮ ደኅንነት እና ስብዕና ግንባታ፣ የማህበረሰብ ጉድኝት ፕሮጀክቶች እና የማህበረሰብ ተጠቃሚነት፣ የትምህርት ክፍሎች እና ተማሪዎች ተሳትፎ በማህበረሰብ ጉድኝት እንዲሁም በ ስቴም (STEM) መርኅ ግብር ዙርያ የተሰሩ ቁልፍ እና ዓቀይት ተግባራት፣ ለቀጣይ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች፣ ፣ ያጋጠሙ ችግሮች እና መፍትሔዎቻቸው አቅርበዋል።
የዩኒቨርሲቲው ቴክኖሎጂ ሽግግር እና ዩኒቨርሲቲ ኢንደስትሪ ትሥሥር ዳይሬክተር መምህር አስመረት ኪዳነ የቁልፍ ተግባራት አፈጻጸም አመላካቾች (KPI) መሰረት በማድረግ የዳይሬክቶሬቱ የ2017 ዓ/ም ሁለተኛ ሩብ ዓመት ቁልፍ እና ዓበይት ተግባራት፣ እያጋጠሙ ያሉ ችግሮች እና በቀጣይ የሚሰሩ ስራዎች በዝርዝር አቅርበዋል፡፡
ከመምህራን በተደረገ ውይይት የተለያዩ ሀሳቦች፣ አስተያየቶች እና ጥያቄዎች የተነሱ ሲሆን በዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች ምላሽ እና ማብራርያ ተሰጥቷል።
በመጨረሻም የዩኒቨርሲቲው የመማር ማስተማር፣ ምርምር፣ ቴክኖሎጂ ሽግግር እና ማኅበረሠብ ጉድኝት ምክትል ፕረዚደንት ዶ/ር ነጋ ዓፈራ ባደረጉት የመዝጊያ ንግግር መምህራን ዕውቀታችሁና ክህሎታችሁ በመጠቀም ተረባርቦና ተቀናጅቶ በመስራት ተቋሙን የሚመጥንና የሚያንፀባርቅ ውጤታማ ስራዎችን መስራት ይጠበቅባችኋል ብለዋል።













********//********************************
ራያ ዩኒቨርሲቲ ፤ የካቲት 25/ 2017 ዓ.ም
ዕውቀት ለማህበረሰባዊ ለውጥ!!!
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አሥፈጻሚ
********//********************************