በ2017 ዓ.ም የሶስተኛ ዙር የድህረ-ምረቃ መርሐ ግብሮች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ምዝገባ ከየካቲት 27 እስከ መጋቢት 01/ 2017 ዓ.ም መከናወኑን ይታወቃል።
በዚሁ መሰረት ፈተናውን ለመፈተን ያመለከታችሁ አመልካቾች ፈተናውን የሚሰጥበት ቀን ዓርብ መጋቢት 05/ 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ጀምሮ መሆኑን አውቃችሁ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በዩኒቨርሲቲው የፈተና ማዕከላት እንድትገኙ እናሳውቃለን፡፡
ማሳሰቢያ፡-
1. ተፈታኞች ወደ ፈተና ማዕከል ስትመጡ ማንነታችሁን የሚገልጽ መታወቂያ መያዝ ይጠበቅባችኋል፡፡
2. ማንኛውም ተፈታኝ ፈተናው ከመጀመሩ 3 ደቂቃ በፊት በፈተና ማዕከል መገኘት ይጠበቅበታል፡፡
3. የሞባይል ስልክ ይዞ በፈተና ማዕከል መገኘት ፈጽሞ የተከለከለ ነው፡፡
4. የፈተና ማዕከላት ምደባ በምዝገባ ፕላትፎርም የሚገለጽ ይሆናል፡፡
መልካም ዕድል ለተፈታኞች!
ራያ ዩኒቨርሲቲ ፤ መጋቢት 02/2017 ዓ.ም
More at
Facebook: https://www.facebook.com/Raya Universityofficial
Website: https://www.rayu.edu.et/
P.O. Box: 92